ጥያቄ(37): ነገር ግን ሙስሊሞች ላይ ከሁለቱ የከፋ አደጋ ያለው የቱ ነው?
መልስ:
ይህ እንግዲህ የሚለካው ሰዎች መካከል በይበልጥ ስርጭት ያለውን ነገር በማየት ይሆናል። አንዳንድ አገሮች ላይ ኮከብ ቆጠራ ምንም አይነት ተፅእኖ አይኖረውም፤ በጭራሽ አያምኑበትም፤ ግምትም አይሰጡትም። ነገርግን እዚህ አገር ላይ ጥንቁልና በስፋት የተሰራጨ ሊሆን ይችላል። ስለዚህም ጥንቁልና እዚህ ቦታ የከፋ አደጋ አለው ማለት ነው። ምናልባትም አንዳንድ ቦታ ደግሞ ነገሩ በዚህ ተቃራኒ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ከሁለቱ ማለትም በተጨባጭ ከምናየው ነገር ስንነሳ ከኮከብ ቆጠራ ይልቅ ጥንቁልና እጅግ አደጋ አለው።