ጥያቄ(24): የስካሁኑ ማብራሪያ ሦ ስተኛው የእምነት ማዕዘን ማብራሪያ ሲሰጡን ነበር እስኪ አሁን ደግሞ አራተኛውን የእምነት ማዕዘን የሆነውን በመልክተኞች ማመን የሚለው ላይ ማብራሪያ ቢሰጡን።
መልስ:
በመልዕክተኞች ማመን ማለት: አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ወደ ሰው ልጆች ባጠቃላይ የአላህን አንቀፅ የሚያነቡና ከተለያዩ እኩይ ተግባራት የሚያጠሯቸው ነቢያት ልኮዋል ብለን እናምናለን። ከነዚህ መልዕክተኞች መካከል የመጀመሪያው ኑሕ ዐለይሂሰላም ሲሆን የመጨረሻው ደግሞ ሙሐመድ ዐለይሂሰላም ናቸው። ከኑሕ በፊት አንድም ረሱል አልተላከም። ከዚህም በመነሳት አንዳንድ የታሪክ ምሁራን ከኑሕ በፊት ኢድሪስ የሚባል ረሱል ነበር የሚለው ንግግራቸው ትክክል እንዳልሆነ እንረዳለን። ምክንያቱም አላህ እንዲህ ይላል፦
ስለ ሸፋዕ (ምልጃ) የሚናገረው ሐዲስ ላይ ፦ “ሰዎች ወደ ኑሕ ይመጡና እንዲህ ይሉታል ፤አንተ ምድር ላይ ለሰዎች መጀመሪያ የተላከው መልክተኛ ነህ።” ስለዚህም ከኑሕ በፊት አንድም የተላከ ረሱል የለም። አላህ እንዲህ ይላል፦
በመጨረሻው ዘመን ኢሳ የሚወረደው በአዲስ መልክት መልክተኛ ሆኖ ሳይሆን በመልዕክተኛው ሙሐመድ ሸሪዓ የሚፈርድ ሆኖ ነው የሚወርደው። በእስላም ሆነ በሌሎች መልክተኞች ላይ በሙሐመድ መልክተኝነት ማመን በነሱ ላይ ግዴታ ነው። አላህ እንዳለው፦
ከዐብዱላሂ ኢብኑ ዐባስ ና ከሌሎች በመጣው ዘገባ መሰረት «ከእናንተ ጋር ላለው (መጽሐፍ) የሚያረጋግጥ መልክተኛ” የተባለው መልክተኛ ሙሐመድ ዐለይሂ ሰላም ናቸው።” በመልክተኞች ማመን አፈፃፀሙ እነሆ እነሱን አስመልክቶ በትክክለኛ ዘገባ የመጡ ታሪካቸውን እናምናለን። እውነተኛነቱን እንቀበላለን። ምክንያቱም ከአላህ ዘንድ የመጣ ስለሆነ። ህግጋትን አስመልክቶ መልክተኛው ሙሐመድ ይዘዋቸው የመጡትንና ሸሪኣቸው የሚያስገድዳቸውን እንጂ ከርሳቸው ውጭ ያሉ ነቢያት በመጧቸው ሕግጋት መስራት በእኛ ላይ ግዴታ አይሆንም።
እያንዳንዱ መልክተኞችን አስመልክቶ አላህ ቁርኣን ውስጥ መልዕክተኛው ደግሞ በሐዲሳቸው ውስጥ ስማቸውን የጠቀሷቸውን በዝርዝር ማመን ግዴታ ይሆንብናል። ስማቸው ሳይሰየሙ የመጡ መልዕክተኞችን አስመልክቶ በመላኢካ እና በመፅሓፍት ማመን ላይ እንዳሳለፍነው እዚህም ላይ እንዲሁ በጥቅሉ ማመን ይኖርብናል።