ጥያቄ(23): ሦስተኛው የእምነት ማዕዘን ላይ ማብራራሪያ መስጠት ይቀረዎታልና ቢዘረዝሩልን።
መልስ:
ሦስተኛ የእምነት ማዕዘን በመፃሕፍት ማመን ሲሆን ከአላህ ወደ መልክተኞች የተወረዱ መፅሓፍት ናቸው። የቁርአን የቀጥታ መልክቱ እንደሚያሳየን ከሆነ አንድም መልክተኛ የለም መፅሐፍ ቢወርድለት እንጂ። ይህን አስመልክቶ አላህ እንዲህ ይላል፦
እንዲህም ይላል፦
በመጽሀፍት ማመን ትክክለኛው መንግዱ እነሆ፦ በጥቅሉ ማመን ያለብን በጥቅሉ ማመን ይኖርብናል። በዝርዝር ማስረጃ የመጣለትን ደግሞ በዝርዝር ማመን ይጠበቅብናል። ተውራት፤ኢንጂል ዘቡር ሱሑፉ ኢብራሂምና ወሙሳ ቁርኣን እነዚህ የምናውቃቸው መፅሓፍት ስለሆኑ በዝርዝር ማመን ይኖርብናል።ከነዚህ ውጭ ያሉ መፅሐፍት በዝርዝ እናምናለን። ምክንያቱ አንዲት ነፍስን አላህ ከአቅሟ በላይ አያስገድዳትምና። ነገር ግን በነዚህ መፅሓፍት በምን መልኩ ነው ማመን ያለብን? ከተባለ በትክክለኛ ዘገባ ወደኛ የመጣውን ምንም በምንም አይነት ሳንጠራጠር ልንቀበልው ይገባል። ምክንያቱም ከአላህ የመጣ መልዕክት ነውና። መፅሓፍቶች በውስጣቸው ያካተቷቸውን ህግጋት አስመልክቶ በቁርኣን ላይ የመጣውን እንጂ ከዚው ውጭ ባሉ መጽሐፍት ውስጥ ያሉ ሕግጋት መስራት ግዴታ የለብንም። ከቁርኣን ውጭ ያሉ መፅሐፍት ውስጥ ትክክል ይሁን አይሁን እርግጠኛ ያልሆንባቸው መልዕክቶች ላይ ትክክል መሆናቸውን እስክናረጋግጥ ድረስ ቆም ማለት ይኖርብናል። ምክንያቱም መጽሓፍቱ መዛባት፤ ቃላት በቃላት መቀየር፤ መልዕክታቸው መቀያየር ጭማሪና ጉድለት ገጥሟቸዋልና።