Back to Top
በልብ ማመንና በዐንደበት መመስከር ልዩነቱ ምንድ ነው? ሁለቱን በአንድ ላይ ማስገኘት ግዴታ ነውን?

ጥያቄ(14): በልብ ማመንና በዐንደበት መመስከር ልዩነቱ ምንድ ነው? ሁለቱን በአንድ ላይ ማስገኘት ግዴታ ነውን?
መልስ:

አዎን።በልብ ማመንና በዐንደበት መመስከር ልዩነቱ ግልፅ ነው።አንዳንድ ሰው በዐንደበቱ ብቻ ቢመሰክርም በቀልቡ አያምንም ለምሳሌ ሙናፊቆች። ሙናፊቆችን አስመልክቶ አላህ እንዲህ ይላል፦

“መናፍቃን በመጡህ ጊዜ «አንተ የአላህ መልክተኛ መኾንህን በእርግጥ (ምለን) እንመሰክራለን» ይላሉ፡፡[አልሙናፊቁን:1]”

አላህ ግ እንዲህ ይላል፦

“አላህም አንተ በእርግጥ መልክተኛው መኾንህን ያውቃል፡፡ አላህም መናፍቃን (ከልብ እንመሰክራለን በማለታቸው) ውሸታሞች መኾናቸውን አላህ ይመሰክራል፡፡” [አልሙናፊቁን:1]

እነዚህ መናፍቃን በልባቸው ሳይሆን በዐንደበታቸው መልክተኛው መልክተኛ መሆኑን መስክረዋል። ምናልባትም አንድ ሰው በቀልቡ አምኖ በዐንደበቱ መመስከር የሚከብደው ይኖራል። በምናየው ውጫዊ ተግባር ተነስተን ፍርድ እንሰጣለን እንጂ ውስጣዊ እምነቱ እኛ ዘንድ ምንም አይፈይደውም። ሆኖም በርሱና በአላህ መካከል ያለውን ጉዳይ አስመልክቶ እኛ የምናውቀው ነገር የለንም። ወይም ደግሞ ሊባል የሚችለው ፍርዱን ወደ አላህ እንተወዋለን። ነገር ግን ዱንያ ላይ ምንም አይጠቅመውም። በዐንደቱ እስካልመሰከረ ድረስ ሙስሊም የሚለው ብያኔ አይሰጠውም። ምናልባት መናገር የሚሳነው ከሆነና ምላሱ ላይ ችግር ኖሮ አሊያም እንዳይናገር የሚከለክለው ነገር ካለ እንደሁነታው ፍርድ ይሰጠዋል። ያም ሆነ ይህ በቀልብም ይሁን በአንደበት መመስከር ግዴታ ነው።




Share

ወቅታዊ