ጥያቄ(108): ከላይ ከጠቀስናቸው ኢማምን ያመከተል ሁኔታዎች ውስጥ እጅግ የከፋው የትኛው ነው?
መልስ:
ኢማምን መቅደም ከሁሉም እጅግ የከፋው ተግባር ነው። ምክንያቱም እንደሰማኸው እርሱን አስመልክቶ ከባድ ዛቻ መጥቶበታል። እንዲሁም አንድ ሰጋጅ ከሰላት ማዕዘናት በአንዱ እንኳ ቢሆን ኢማሙን ቀድሞ ከሰገደ ሰላቱ ተቀባይነት የለውም የሚለው ትክክለኛ እና ሚዛን የሚደፋ አቋም ነው። ምክንያቱም ኢማሙን ቀድሞ ከሰገደ ሰላቱ ውስጥ የተከለከለ ድርጊትን ፈፅሟል።
ሸሪዓዊ ከሆኑ ጥቅላዊ መርሆች መካከል፤ዒባዳ ውስጥ የተከለከለ ተግባር የፈፀመ ዒባዳው ተቀባይነት የለውም የሚለው ይገኝበታል።