Back to Top
ስለ ሰላት ሁክም፣መስፈርቶች እንዲሁም ማዕዘናት እና ዋጂባት ተነጋግረናል። በተጨማሪም ስለሱጁድ ሰህውም አውርተናል። ስለ ሰላት ጀመዓ ሁክም ትኩረት አድርገን ልንጠይቅዎ እንሻለን።

ጥያቄ(106): ስለ ሰላት ሁክም፣መስፈርቶች እንዲሁም ማዕዘናት እና ዋጂባት ተነጋግረናል። በተጨማሪም ስለሱጁድ ሰህውም አውርተናል። ስለ ሰላት ጀመዓ ሁክም ትኩረት አድርገን ልንጠይቅዎ እንሻለን።
መልስ:

የጀመዓ ሰላትን አስመልክቶ ከአምልኮት ዘርፎች መካከል እጅግ የላቀው፤ ጠንከር ያለና በላጭ ተግባር መሆኑ ላይ የኢስላም ሊቃውንቶች የጋራ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

አላህ በቁርኣኑ ጀመዓ ሰላትን በፍራቻ ወይም ጦርነት ላይ ሳይቀር አዞታል።

አላህ አዘወጀለ እንዲህ ይላል፦

“በውስጣቸውም በኾንክና ሶላትን ለእነርሱ ባሰገድካቸው ጊዜ ከእነሱ አንዲት ጭፍራ ካንተ ጋር ትቁም። መሣሪያዎቻቸውንም ይያዙ። በግንባራቸውም በተደፉ ጊዜ ከስተኋላችሁ ይኹኑ። (እነዚህ ይኺዱና) ያልሰገዱትም ሌሎቹ ጭፍሮች ይምጡ፡፡ ከአንተም ጋር ይስገዱ፡፡ ጥንቃቄያቸውንና መሣሪያዎቻቸውንም ይያዙ።” [አኒሳእ:102]

በመልክተኛው ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ንግግር ላይ ሰላተል ጀመዓ ዋጂብ መሆኑን የሚጠቁሙ እጅግ በርካታ ሐዲሶች ተዘግበው መጥተዋል።

ለአብነት ያህል፤ መልክተኛው ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦

 “(ከእለታት ባንዱ ቀን)ሰላት ኢቃም እንዲደረግለት፣ከዚያም ከመሃላቸው አንዱ እንዲያሰግድ ፣ከዚያም የእንጨት ችቦ የያዙ ሰዎችን ይዤ ሰላት በህብረት ለመስገድ ወደ መስጊድ የማይመጡ ሰዎች ቤታቸው ውስጥ ሳሉ ቤታቸውን ላቃጥል አስቤ ነበር።”

መልክተኛው ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦

 “(በቂ ሸሪዓዊ )ምክንያት ያለው ሲቀር፤ አዛን ሰምቶ ወደ ሰላት መስገጃ ያልመጣ ሰላት የለውም።”

እንዲሁም አንድ ማየት የተሳነው ሰው ወደ መልክተኛው ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም መጥቶ ቤቱ መስገድ ላይ እንዲያገሩለት ሲያስፈቅዳቸው፦

“አዛን ትሰማለህን?” ሲሉ ጠየቁት፤ እርሱም፦ “አዎን” በማለት መለሰላቸው። እርሳቸውም፦ “እንግዲያውስ ለሰላቱ ጥሪ ምላሽ ስጥ።” አሉት።

ዐብዱላሂ ኢብኑ መስዑድ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፦ “ሙናፊቅ አሊያም በሽተኛ ካልሆነ በስተቀር ሰላተል ጀማዓን ባለመስገድ ወደኋላ የሚቀር በመሀከላችን እንደሌለ ታውቃላችሁ። ምናልባትም አንድ ሰው ከመታመሙ ብዛት መሄድ አቅቶት በሁለት ሰዎች መካከል እየተንፏቀቀ ከመጣ በኋላ ሰፍ ላይ እንዲቆም ይደረግ ነበር።”

ሌላው ደግሞ ጤናማ እይታ ያለው የሰላተል ጀመዓን ዋጅብነት ይረዳል። ሙስሊሙ አንድ ማህበረሰብ ነው። የሙስሊሙ አንድነት ተጠብቆ  ሊዘልቅ የሚችለው ደግሞ  በህብረት በመሆን ዒባዳን መፈፀም ሲችሉ ብቻ ነው። ከአምልኮት ዘርፎች መካከል ደግሞ የላቀው፣ጠነከር ያለ ትዕዛዝ የመጣበትና በላጭ ተግባር ሰላት ነው። ስለሆነም ህዝበ ሙስሊሙ ሰላትን ለመፈፀም በህብረት መሰባሰብ ይኖርበታል።

  የጀመዓ ሰላትን አስመልክቶ ከአምልኮት ዘርፎች መካከል እጅግ የላቀው፤ ጠንከር ያለና በላጭ ተግባር መሆኑ ላይ የኢስላም ሊቃውንት የጋራ ስምምነት ላይ ከመድረሳቸው ጋር የጀመዓ ሰላት ለሰላት መስፈርት ነው? ወይስ ከወንጀል ጋር ብቻውን መስገድ ይቻላል? በሚለውና  ሌሎች መሰል ጉዳዮች ላይ ኺላፍ አለ።

ሆኖም ትክክለኛውና ሚዛን የሚደፋው አቋም ፦ የሰላት መስፈርት የሚለው አቋም ትክክል አይደለም። የሰላት ዋጂብ ነው የሚለው ትክክለኛ ነው። ሆኖም ያለምንም ምክንያት (ዑዝር) ሰላተል ጀመዓ የተወ ወንጀል አለበት። ሰላተል ጀመዓ የሰላት ሸርጥ (መስፈርት) ላለመሆኑ ማስረጃው፤

መልክተኛው ዐለይሂ ሰላት ወሰላም በጀመዓ (በህብረት) የሚሰገድ ሰላት በግል ከሚሰገድ ሰላት እንደሚበልጥ ተናግረዋል።

 ይህ ደግሞ በግል መስገድ ደረጃ ወይም ተቀባይነት እንዳለው ያሳያል። ምክንያቱም በደረጃ ማበላለጣቸው ሰላቱ በግልም ቢሰገድ ተቀባይነት እንዳለው ይጠቁማል።

ያም ሆነ ይህ! ለአቅመ አደም የደረስ ወንድ በሙሉ ሰላትን በህብረት ለመስገድ መስጂድ መምጣት ግዴታ ይሆናል።(ይጠበቅበታል)።




Share

ወቅታዊ