Back to Top
በተጨማሪም ሱጁድ ሰሕው የሚያስደርጉ ስህተቶች እና ቦታዎቻቸው ማወቅ እንፈልጋለን እና (ቢገልፁልን)?

ጥያቄ(102): በተጨማሪም ሱጁድ ሰሕው የሚያስደርጉ ስህተቶች እና ቦታዎቻቸው ማወቅ እንፈልጋለን እና (ቢገልፁልን)?
መልስ:

ሱጁድ ሰህው የሚያስደርጉ ሰበቦች በጥቅሉ ሦስት ናቸው። እነሱም፦ የሰላት ተግባሮችን መጨመር፣መቀነስ እና ተግባሮችን ፈፅሜያለሁ? ወይንስ አልፈፀምኩም? ብሎ መጠራጠር ናቸው።

መጨመር ማለት፤ ሰጋጅ ሰላት ውስጥ ሩኩዕን ወይም ሱጁድን ወዘተ ሆን ብሎ ከጨመረ ሰላቱ ይበላሽበታል። ምክንያቱም ሆን ብሎ ሰላቱ ላይ ተጨማሪ ተግባር መፈፀሙ አላህና መልክተኛው ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ካዘዙት ተግባር ውጭ ስለፈፀመ ሰላቱ ተቀባይነት የለውም። መልክተኛው ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦

 “ትእዛዛችን የሌለበትን ስራ የሰራ በርሱ ላይ ተመላሽ ነው።”

ሆኖም በመርሳት ሰላት ውስጥ ከጨመረ ሰላቱ አይበላሽም። ነገር ግን ካሰላመተ በኋላ ሱጁድ ሰህው ማድረግ ይኖርበታል። ለዚህም ማስረጃው የሚከተለው ሐዲስ ነው፦

አቡሁረይራ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፦ “መልክተኛው ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሰላታቸው አንዱ ዐስር ወይም ዙሁር ላይ ሁለት ረከዓ ካሰገዱ በኋላ አሰላመቱ። መርሳታቸውን ሲነገራቸው የተቀሩትን ሁለት ረከዓዎች አሰግደው ካሰላመቱ በኋላ ሁለት ሱጁድ አደረጉ።”

በተጨማሪም ዐብዱላህ ኢብኑ መስዑድ ረዲየላሁ ዐንሁ ባስተላለፉት ሐዲስ ላይ መልክተኛው ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም በመርሳት ዙህርን አምስት ረከዓ አሰገዷቸው ካሰላመቱ በኋላ “ሰላቱ ላይ ተጨማሪ ተደረገን?” ሲሉ ጠየቋቸው። መልክተኛውም ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም “ምን ተከሰተ?” ሲሉ ጠየቋቸው እነሱም፦ “አምስት ረከዓ አሰገዱን።” አሏቸው። ወዲያውኑ ወደ ቂብላ በመዞር ሁለት ሱጁዶችን ወርደው አሰላመቱ።

ማጉደልን አስመልክቶ ደግሞ፤ይህ ማለት ሰጋጁ ከሰላት ማዕዘናት አንዱን ካጓደለ እሱን አስመልክቶ ማድረግ የሚጠበቅበት ከሁለት ነገሮች አንዱን ይሆናል። ሁለተኛው ረከዓ ጋር ካልቀጠለ ወደ ተወው የሰላት ማዕዘን በመመለስ መስገድ ይጠበቅበታል። ነገር ግን ሁለተኛው ረከዓ ላይ ከደረሰ ሁለተኛው ረከዓ  የመጀመሪያው ረከዓ ሆኖ ይቆጠርለታል። ሁለቱም ድርጊቶች ላይ ካሰላመተ በኋላ ሱጁድ ሰህው ይወርዳል።

ምሳሌውም ፦ የመጀመሪያው ረከዓ ላይ ሁለተኛውን ሱጁድ እና በሁለቱ ሱጁዶች መካከል መቀመጥ ረስቶ ወደ ሁለተኛው ረከዓ ቢቆም ፋቲሃን ማንበብ እንደጀመረ ሱጁድ እና መቀመጥን መርሳቱ ትዝ አለው፤ በዚህን ጊዜ ወዲያውኑ በሁለቱ ሱጆዶች መካከል የረሳውን መቀመጥ ሊመልስ ዘንድ ቁጭ ማለት አለበት ከዚያም ሱጁድ ያደርጋል። ከዚያም የተቀረውን ሰላት ለማሟላት ብድግ ይላል ካሰላመተ በኋላ ሱጁድ ሰህው ያደርጋል።

ዋጂብ ተግባርን ከቀነስ ደግሞ፤ዋጂብን ትቶ ወደ ሚቀጥለው ቢሸጋገር፤ለምሳሌ፦ “ሱብሃነ ረቢየል አዕላ” ረስቶ ሱጁድ ካደረገ በኋላ መርሳቱ ትዝ ቢለው፤ ይህ ሰው በዚህ ተግባሩ ከሰላት ዋጂባት መካከል አንዱን  በመርሳት ትቷል። ስለሆነም ሰላቱን ሳያቋርጥ ይቀጥላል። ከዚያም ካሰላመተ በኋላ ሱጁዱ ሰህው ያደርጋል።

ሰላት ውስጥ ጥርጣሬን አስመልክቶ ከሆነ ደግሞ፤ ማለትም የሰላት ተግባሮች ላይ በመጨመር አሊያም በመቀነስ ላይ ቢጠራጠር። ለምሳሌ፦ ሦስት ነው? ወይስ አራት? ረከዓ የሰገድኩት ብሎ ቢጠራጠር። እዚህ ላይ ከሁለት ሁኔታዎች የዘለለ አይሆንም። አንደኛው፤ መጨመሩ ወይም መቀነሱ ላይ ያለው ግምት ካዘነበለ ወዳዘነበለበት በመጓዝ በዚያ ላይ ይገነባል። እርሱም ትንሹ ቁጥር ሲሆን በዛው ይቀጥላል ከዚያም ከማሰላመቱ በፊት ሱጁድ ያደርጋል።

ለዚህም ምሳሌው፦ ሰውየው ዙህርን እየሰገደ ሳለ አራተኛው ወይም ሦስተኛው ረከዓ ላይ መሆኑ ላይ እርግጠኛ አልሆነም ነገር ግን ሦስተኛው ረከዓ ነው የሚለው ልቡ ላይ ቢያመዝን አንድ ረከዓ በመስገድ ሰላቱን ያሟላል ከዚያም ካሰላመተ በኋላ ሱጁድ ሰህው ያደርጋል። ሁለቱም ግምቶች እኩል የሚሆንበት ምሳሌው፦ የሚከተለው ነው፤ ሰውዬው ዙህር እየሰገደ ሳለ ሦስተኛው ረከዓ ይሁን አራተኛው የሚል ጥርጣሬ ቢያድርበትና ከሁለቱ አንዱ ላይ ግምቱ ካላመዘነ በዚህን ጊዜ ትንሹን ቁጥር ላይ እርግጠኛ መሆን አለበት ሦስተኛው ረከዓ እንደገነ በመቁጠር አራተኛውን ረከዓ በመስገድ ከማሰላመቱ በፊት ሱጁድ ሰህው ያደርጋል።

ከዚህም ማብራሪያ ግልፅ የሚሆንልን ነገር ቢኖር፦

 ከሰላት ዋጂባት መካከል አንዱን ሲተው እና ረከዓዎች ላይ ጥርጣሬ አድሮበት ከሁለት አንዱ ሳያመዝን ሲቀር ሱጁድ ሰህው ከማሰላመት በፊት ይሆናል።

ሰላት ውስጥ ጭማሪ ተግባሮች ሲከሰቱና ጥርጣሬ ላይ ወደ አንዱ ሲያመዝን ሱጁዱ ሰህው የሚደረገው ከሰላት በኋላ ይሆናል።




Share

ወቅታዊ