Back to Top
የሰላት ዋጂባት ካወቅን አይቀር የሰላት ሱናዎችንም ማወቅ እንሻለን።

ጥያቄ(101): የሰላት ዋጂባት ካወቅን አይቀር የሰላት ሱናዎችንም ማወቅ እንሻለን።
መልስ:

አንድ ሰጋጅ የሰላት ማዕዘናት፣ዋጂባት ካወቀ የተቀሩት ተግባሮች የሰላት ሱናዎች መሆናቸውን ማወቁ አያዳግተውም። ሰላት ውስጥ ሱና ከሆኑ ተግባሮች መካከል፦

ሩኩዕና ሱጁድ ላይ ከአንድ በላይ ተስቢህ ማድረግ ማለትም ሩኩዕ ላይ “ሱብሃነ ላሂ አል ዐዚም” ሱጁድ ላይ ደግሞ “ሱብሃነ ረቢየል አዕላ” የሚለው ዚክርን ከአንድ በላይ ማድረግ።

ከነዚህ ተግባሮች መካከል በተጨማሪም፤ ሰላት ውስጥ የሚገኘው አቀማመጥ። ሁሉ ሰላቶች ላይ “ኢፍቲራሽ” የሚባለውን አቀማመጥ መቀመጥ ይኖርበታል። “ኢፍቲራሽ” ማለት፦ ቀኝ እግሩን ወይም ተረከዙን መሬት ላይ በመትከል በግራ እግሩ ላይ በቂጡ መቀመጥ ማለት ነው። ይህ ባለ ሁለት ረከዓ ሰላቶችን የሚመለከት ሲሆን ባለ አራት ረከዓ ሰላቶች ላይ ደግሞ  አራተኛው ረከዓ ላይ የምንቀመጠው አቀማመጥ “ተወሩክ” ይባላል። “ተወሩክ” ማለት ደግሞ ቀኝ እግሩን መሬት ላይ በመቸከል ግራ እግሩን በቀኙ ባት በኩል ያሳልፍና በቂጡ መሬት ላይ ይቀመጣል።

ሰላት ውስጥ ሱና ከሆኑ ተግባሮች መካከል፦ ተክቢረተል ኢህራም ላይ ፣ሩኩዕ ላይ ፣ከሩኩዕ ብድግ በሚባልበት ጊዜ እና ከሁለተኛው ተሸሁድ በመነሳት ሦስተኛው ረከዓ ለመስገድ በሚቆምበት ሰዓት ወደ ትከሻው ወይም ጆሮዎቹ ትይዩ መዳፎችን ማንሳት ይገኝበታል። የሰላት ሱናዎች እነዚህ ብቻ ሳይሆኑ ብዙ ናቸው የፉቀሃዎችን መፅሃፍት ያገላበጠ ይደርስበታል።




Share

ወቅታዊ